የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከዚህ በታች በተገለጸው የስራ መደብ ላይ ብቁ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የመንገድ መሰረተ ልማት ክትትልና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር ብዛት፡ 1 የመደብ ቁጥር፡ ትራ/ሚ-47 ደረጃ፡ XVII ደመወዝ፡ 12,579.00 ተፈላጊ ችሎታ፡ በሲቪል ምህንድስና፣ በአርክቴክቸር፣ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የትምህርት መስክ እና 10 ዓመት በአሰራር ጥራት ኦዲት፣ የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን የሰራ/ች ከዚህ በላይ የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከማመልከቻና CV ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል። የመመዝገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ዋናው ፖስታ ቤት በሚገኝበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።