ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ መስፈርት የሚያሟሉትን አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል። የስራ መደብ፡ የመረጃ ስራ አመራር ባለሙያ I ደመወዝ፡ 3,526 ብዛት፡ 2 የስራ ቦታ፡ ልደታ የቅጥር ሁኔታ፡በቋሚነት አግባብ ያለው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ፡ በስታቲስቲክስ፣በኢኮኖሚክስ፣ በስራ አመራር፣ MIS፣ የመጀመሪያ ዲግሪ 0 ዓመት ያለው/ያላት ማሳሰቢያ፡ - የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ከLevel 1 እስከ Level 4 ከሆነ የሲኦሲ ውጤት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 504 ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።